መጋቢት 24/2018
በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቀላል የማይባል ችግር እንደሚያጋጥማቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡
የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ እነሱን ተቀብሎ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አለማግኘት፣ የቁሳቁስ አለመሟላት፣ በስራ ቅጥር ወቅት እድል አለማግኘት እና በሌሎች ፈተናዎች እንደሚያልፉ ይነገራል፡፡
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች እኩል የማይማሯቸው ትምህርቶች በመኖራቸው ተወዳዳሪነታችንን ይቀንስብናል ብለዋል።
በዚህም ምክንያት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚቸገሩ አንስተዋል።
Comments