ነሐሴ 7፣2016
በአጠቃላይ 45 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያላቸው ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ለውጭ ምንዛሪ ግብይት ሱቅ እንዲከፍቱ ተፈቅዷል፡፡
ሱቆቹ በመላው ኢትዮጵያ ይከፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጥቁር ገበያውን በማክሰም ረገድ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ በተመለከተ እና ከጥቁር ገበያ ውጭ ከባንኮችም መወዳደር የሚጠበቅባቸው የእነዚሁ ሱቆች ባለቤት ማን ሊሆን ይችላል?
በጉዳዩ ላይ የምጣኔ ሐብት ባለሞያ አነጋግረናል፤ ባለሞያው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፤
• ከመስፈርቱ ውስጥ 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል እና 30 ሚሊዮን ብር በዝግ አካውንት የሚቀመጥ ካፒታል ያለው ባለሀብት የምንዛሬ ሱቅ ግብይት መክፈት ይችላል፡፡
• በባንኮች ውስጥ ፍላጎትን የሚመጥን የውጭ ምንዛሬ ክምችት እስካልኖረ ድረስ ጥቁር ገበያውን ማክሰም አዳጋች ነው፡፡
• በቂ ካፒታል ካላቸው በጥቁር ገበያው ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ በህጋዊ መንገድ የምንዛሬ ሱቅ ለመክፈት እድል ስለሚያገኙ ጥቁር ገበያው እንዲሳካ ህጋዊ ሱቅ እንዲከፍቱ መፍቀዱ እድል ይሰጣል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
#የውጭ_ምንዛሪ_ግብይት_ሱቆች #ጥቁር_ገበያ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments