TRACK
በእርዳታ ሰበብ የራሳቸውን ፖሊሲ ለማስፈፀም እና የሀገር ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ድርጅትችን እየተቆጣጠርኩ ነው ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ
00:00
ሐምሌ 30፣2016
በእርዳታ ሰበብ የራሳቸውን ፖሊሲ ለማስፈፀም እና የሀገር ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ድርጅትችን እየተቆጣጠርኩ ነው ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡
በኢትዮጵያ በተለያየ ችግር መነሾነት ለእርዳታ የተዳረጉ ሰዎችን ለመርዳት በሚል በህጋዊነት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ሀገር በቀል እና የውጭ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡
በተለይም መሰረታቸው ውጭ ሀገራት ያደረጉት እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በእርዳታ ሰበብ፤ የራሳቸውን ፍላጎት ይዘው የሚመጡ ናቸው ሲባል ይሰማል፡፡
ድርጅቶቹ የመጡበትን ሀገራት ፖሊሲን በእጃዙር በኢትዮጵያ ለማስፈፀም ይጥራሉ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት የመዳፈር ተግባራትም ላይ ይሰማራሉ ተብለው ይጠረጠራሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን እንደሚለው ከሆነ የሀገር ክብር የማይጠብቁ ተግባራት ላይ የሚሰማሩት ላይ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል፡፡
በባለስልጣኑ የዋና ደይሬክተር ፅ/ቤት ሀላፊ በፍቃዱ ወልደሰንበት እንደሚሉት ማንኛውም እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ብርቱ ክትትል ይደረጋል ብለውናል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በያሬድ እንዳሻው
Comments
00:00