ነሐሴ 24፣2016
በኢትዮጵያ በሚደርሱ ሰው ሰራሽም ይሁን የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተጎጂዎችን ቁጥር አጋንነው የሚቀርቡ፤ የሚመደበውን እርዳታም ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉትን ተጠያቂ የሚያደርግ ፖሊሲ ሊፀድቅ ነው፡፡
ተደጋግመው እየደረሱ ያሉ የጎርፍና #የመሬት_መንሸራተት አደጋዎች፣ በየአካባቢው ባለው ግጭትና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ጠባቂ መሆናቸው ይነገራል፡፡
ለእነዚህ ተረጂዎች የሚመደብ የእለት ደራሽ #ምግብ እና ሌላውም ቁሳቁስ በአግባቡ መድረሱን የሚቆጣጠር አካል እስካሁን አልነበረም፡፡
ተረጂዎቹም በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ በቂ ድጋፍ አልተደረገልንም የሚል ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡
ለተረጂዎቹም እፎይታን የሚሰጥ፤ የሚመደበውን እርዳታም ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ፤ የተረጂዎቹን ቁጥር አጋንነው የሚያቀርቡ የመንግስት ሹመኞችንና ባለሙያዎች በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ የፖሊሲ ረቂቅ መዘጋጀቱንና በቅርቡ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም ስራውን ሲጀምር እንደሚፀድቅ የፌድራሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አታለል አቡሃይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
Comments