ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ የታክስ ቅሬታ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተናገረ
TRACK

ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ የታክስ ቅሬታ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተናገረ

Avatar

ግንቦት 8 2017

ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ የታክስ ቅሬታ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ከእነዚህ መዝገቦች ገሚሶቹ ለመንግስት የተወሰኑ ገሚሶቹ ደግሞ ለቅሬታ አቅራቢዎቹ ተወሰኑ ናቸው ተብሏል፡፡

የግብር አከፋፈልና የጉምሩክ ጉዳዮችን በተመለከተ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የሚያቀርባቸው ቅሬታዎች በመመርመርና ሁለቱን በማከራከር በገለልተኝነት ፍትሃዊ ውሳኔዎችን እየሰጠ መሆኑን ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

በዚህም ባለፉት 9 ወራት ከቀረቡለት 1ሺህ 144 የግብር አቤቱታ መዝገቦች ከ3.3ቢሊዮን ብር በላይ በሚያወጡ 686 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar