በፕሪቶሪያው የሰለም ስምምነት የፌደራል መንግስት ለህውሃት ለመፈፀም የገባው ስምምነት ምንድነው?
TRACK

በፕሪቶሪያው የሰለም ስምምነት የፌደራል መንግስት ለህውሃት ለመፈፀም የገባው ስምምነት ምንድነው?

00:00

ነሐሴ 16፣2016

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ሕወሃት) በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የቀድሞ ህጋዊ ሰውነቴ ይመለስልኝ ሲል፤ መንግስት በበኩሉ የሕወሃትን የህግ ሰውነት እና ምዝገባ ጉዳይ በስምምነቱ ውስጥ የወሰድኩት የተለየ ኃላፊነት አልያም ግዴታ የለም ብሏል፡፡

ሕወሃት በበኩሉ ስምምነቱ እንዲህ ባለ መልኩ መተረጎም የለበትም ብሏል፡፡

ይህም በሁለት በተከፈለው ህወሃት እና በፌደራል መንግስት መካከል አለመስማማትን የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በፕሪቶሪያው የሰለም ስምምነት ሲፈረም የፌደራል መንግስት የወሰደው ግዴታ የህወሃት የሽብርተኝነት ፍርድ እንዲነሳ ሂደቱን ቀና ማድረግ እንደሆነ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተናግሯል፡፡

Comments

00:00