ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በወር 19 ሚሊየን ዶላር ያህል እንደምታጣ ጥናቱ አሳይቷል
TRACK

ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ በወር 19 ሚሊየን ዶላር ያህል እንደምታጣ ጥናቱ አሳይቷል

Avatar

ሰኔ 18 2017

የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ በርካታ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።

ኮንትሮባንድ፣ የግብይት ስርአቱ ደካማ መሆን፣ የእንስሳት ማቆያ ቦታዎች በበቂ መጠን አለመኖር እንዲሁም የህክምና እና የዕርድ ማዕከላት በሚገባው ደረጃ አለመገኘት የዘርፉ ችግሮች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።

በዚህም ምክንያት እስከ 150 ሚሊየን ዶላር ሲገኝበት ነበር የሚባለው የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ንግድ እያሽቆለቆለ መጥቶ 2014 እና 2015 ላይ 17 ሚሊየን ዶላር ወርዷል።

በሶስት የመውጫ በሮች በተደረገ ጥናት በቀን ከ1200 በላይ የቁም እንስሳት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር እንደሚወጡ በአንድ ወቅት ይፋ በሆነ ጥናት ተመልክቷል።

በዚህም ኢትዮጵያ በቀን ከ630 ሺህ ዶላር በላይ ፤ በወር ደግሞ 19 ሚሊየን ዶላር ያህል በህገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ምክንያት እንደምታጣ ጥናቱ አሳይቷል።

Comments

Avatar