ህዳር 25፣2017
በትግራይ ክልል የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ፡፡
በትግራይ ደቡባዊ ዞን በ650 ሄክታር የማሽላ ሰብል ላይ የተከሰተው #የግሪሳ_ወፍ መንጋ እስካሁን 320 ሄክታር የማሽላ ሰብልን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተነግሯል፡፡
ይህንን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት የክልሉ የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ትንተና ኃላፊው አቶ ገብረአብ ገ/መድን ናቸው፡፡
የወፍ መንጋው ወደ ቆላማው የማሽላ አምራች #የትግራይ_ወረዳዎችም እየተስፋፋ ነው ተብሏል፡፡
Comments