ያንጎ ኩንባያ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ያለኝ ተፈላጊነት በፍጥነት እያደገ መጥቷል አለ
TRACK

ያንጎ ኩንባያ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ያለኝ ተፈላጊነት በፍጥነት እያደገ መጥቷል አለ

Avatar

ነሐሴ 8፣2016

መሰረቱን ከሩሲያ አድርጎ ዋና መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ያንጎ ኩንባያ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ያለኝ ተፈላጊነት በፍጥነት እያደገ መጥቷል አለ፡፡

ያንጎ የትራንስፖርት አቀላጣፊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በኢትዮጵያ ገበያ መስራት የጀመረው በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የያንጎ አፕልኬሽን ወይንም መተግበሪያ በስልካቸው ላይ የጫኑ ሰዎች 1 ሚሊዮን ማለፋቸውን ኩባንያው ተናግሯል፡፡

በያንጎ የኢትዮጵያ ሀላፊ ዶ/ር ዓቅናለም አበበ አንድ ጊዜ የያንጎ መተግበሪያ በስልኩ ላይ የጫነ ሰው ድርጅቱ በሚሰራባቸው በላቲን አሜሪካም፣ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ነግረውናል፡፡

በአፕልኬሽን ወይንም መተግበሪያ ብቻ የያንጎን አገልግሎት የሚያገኙ ሰዎች ብዛት ከ1 ሚሊዮን መብለጡን የተናገሩት ሀላፊው ከጥር ወዲህ ብቻ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በአራት እጥፍ አድጓል፣ ይህም ድርጅቱ ከጠበቀው በላይ ነው ብለዋል፡፡

ዋና መቀመጫው በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ያደረገው ያንጎ በኢትዮጵያ በአልጀሪያ፣ አንጎላ፣ በቺሊ፣ በኖዌይ፣ በሩሲያ፣ ቱርክ፣ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና በሌሎችም ሀገሮች ይሰራል፡፡

Comments

Avatar