ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ
TRACK

ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ

Avatar

ሰኔ 10 2017

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው በምርመራ ወቅት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡

አዋጁ በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆኖ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ይላል።

የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ(ዶ/ር) በአዋጁ 5/15 ላይ የቀረበው ዐረፍተ ነገር ትንሽ ከባድ መስሎ እንደታያቸው ተናግረው አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እንደዚህ ዓይነት አዋጅ በተለይ ሽብርን ለመከላከል ለሀገራችን ያስፈልጋታል ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar