የኦሮሚያ ክልል መንግስት ቀበሌዎችን በማጠናከር ለህዝቡ የሚሰጠውን አገልግሎት እንደሚያሻሽል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሣ ተናገሩ
TRACK

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ቀበሌዎችን በማጠናከር ለህዝቡ የሚሰጠውን አገልግሎት እንደሚያሻሽል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሣ ተናገሩ

00:00

ሐምሌ 15፣ 2016

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ቀበሌዎችን በማጠናከር ለህዝቡ የሚሰጠውን አገልግሎት እንደሚያሻሽል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሣ ተናገሩ።

ወደ ከተማ የሚያድግ የክልሉ አካባቢ በመጪዎቹ አመታት እንደማይኖርም ርዕሰ መስተዳድሩ በአዳማ እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሣ የክልሉን የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017ን ዕቅድ ለጨፌው አቅርበዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎም የክልሉ ምክር ቤት ጨፌ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የመዋቅር ጥያቄዎች እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ በክልሉ የሚታዩ ችግሮች ከእነዚህ መካከል ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽ የክልሉ መንግስት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ቀበሌዎችን እንደሚያጠናክር ግን ደግሞ
ከተማ እንሁን የሚሉ ጥያቄዎችን ለመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት እንደማያስተናግድ ተናግረዋል።

Comments

00:00