መጋቢት 21/2018
በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ አቅርቦት አግኝተው ምርታማ እንዲሆኑ የፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ከሰባት ትሪሊዮን ብር በላይ ብድር ፈሰስ ማድረግ እንዳለባቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ይሁንና የሚቀርበው ብድር ከሚያስፈልገው ከግማሽ በታች መሆኑን ከሰሞኑ የብሔራዊ ባንክ ያወጣው ሪፖርት አሳይቷል፡፡
እንደ ማሳያ የግብርናው ዘርፍ በየዓመቱ ከሁለት ትሊዮን ብር በላይ ብድር እያስፈለገው ያገኘው ግን 8 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ካገኘው ብድሩ መካከልም አብዛኛው ለማዳበሪያ ማስመጫ የተሰጠ ብድር መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አሳይቷል፡፡
ለአምራች ኢንዱስትሪውና ቤት መግዛት ለሚፈልጉም የሚቀርበው ብድርም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡
በተለይ ለቤት ገዥዎች የሚያስፈልገው ብድር ቢቀርብ እንኳን በተለይ ተቀጣሪው የመበደርና ብድሩን የመመለስ አቅም የለውም፡፡
በሌላ በኩል የቁጠባም ሆነ የብድር ተጠቃሚዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በፋይናንስ ተቋማት ለተቀማጭነት ከተቆጠበ ገንዘብ 60 በመቶው በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሀብት መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አሳይቷል፡፡
ለግለሰቦችም ሆነ ለሀገር እድገት የቁጠባም ሆነ የብድር አቅም ከፍ ማለት እንዳለበት እሙን ነው፤ ሪፖርቱ የሚያሳየው ደግሞ ተቃራኒው ነው፡፡
መፍትሄው ምንድነው? የፕራግማ ካፒታል መስራችና የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ባለሙያውን አቶ መርዕድ ፍቅረዮሐንስን ጠይቀናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ትዕግስት ዘሪሁን ያዘጋጀችውን በንጋቱ ሙሉ
Comments