ከሚወለዱ 10,000 ህፃናት ውስጥ 80 የሚሆኑት የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ያጋጥማቸዋል ተባለ፡፡
TRACK

ከሚወለዱ 10,000 ህፃናት ውስጥ 80 የሚሆኑት የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ያጋጥማቸዋል ተባለ፡፡

Avatar

ጥር 28/2018

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ 10,000 ህፃናት ውስጥ 80 የሚሆኑት የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር ወይም ሀይድሮሴፋለስ ችግር ያጋጥማቸዋል ተባለ፡፡

ችግሩ በሀገሪቱ የሚገባውን ያህል ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ በማህበረሰብ ላይ የሚያደርሰው ጫና ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም የህክምና ኮሌጅ የህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሱራፌል መኮንን ስለ ህመሞቹ ይህንን ያስረዳሉ፡፡

ስፓይና ቢፊዳ ( #Spina_Bifida ) ማለት ከነርቨ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት (ክፍተት) ነው።

በአብዛኛው ጊዜ ስፓይና በፊዳ ያለባቸው ሕጻናት ፈሳሽ በአጎላቸው ወስጥ ስለሚከማች ሃይደሮ ሴፋለስም ያጋጥማቸዋል።

Comments

Avatar