''አፍሪካ ውስጥ ያለው የትምህርት ምዘና ሥርዓት ወጥ ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው'' የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
TRACK

''አፍሪካ ውስጥ ያለው የትምህርት ምዘና ሥርዓት ወጥ ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው'' የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

Avatar

ነሀሴ 20 2017

አፍሪካ ውስጥ ያለው የትምህርት ምዘና ሥርዓት ወጥ ከተደረገ ሰዎች ወደ የትኛውም የአህጉሪቱ ክፍል ሄደው የጀመሩትን ትምህርት እንዲቀጥሉ ይረዳል ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተናገረ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዳለው አሁን ባለው የምዘና ሥርዓት አንድ ተማሪ ከኢትዮጵያ ወጥቶ በሌሎች የአፍሪካ ሀገር ትምህርቱን ካቆመበት ለመቀጠል ይቸገራል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ(ዶ/ር) አፍሪካ ውስጥ ያለው የትምህርት ምዘና ሥርዓት ወጥ ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ማዕቀፍ ለመተግበር እንዲቻል እየተደረገ ባለው የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ጉባኤ ምክክር ይደረግበታል ያሉ ሲሆን ተሳታፊ ሀገራትም በአፍሪካ ህብረት በኩል ሀገራቸው ውስጥ እንዲተገበር ለማድረግ ቃል የሚገቡበት ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

Comments

Avatar