የካቲት 11/2018
በአዲስ አበባ ባንኮችን፣ የግል ተቋማትን፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሌላም ሌላም እንዲጠብቁ ሀላፊነት ወስደው፣ ህጋዊ ፍቃድ ተቀብለው፣ ሰራተኛ ቀጥረው የሚያስጠብቁ የግል ኤጅንሲዎች ቁጥር 250 ደርሷል ተብሏል።
በእነዚህ ኤጀንሲዎች ስር ተቀጥረው ዩኒፎርም ለብሰው፣ ዱላ ታጥቀው የሚጠብቁት የመስሪ ቤቱ ንብረት እንዳይዘረፍ፣ ተቋሙ ጥቃት እንዳይደርስበት በር ላይ ቁመው የሚቆጣጠሩ፣ ሰራተኛው ሲገባ ፍትሸው የሚያስገቡ፣ ሲወጣ አይተው የሚሸኙ ካላቸው ሀላፊነት ከተሰጣቸው የስራ ድርሻ አንጻር የሚከፈላቸው ደመወዝ ለእለት ጉርስ የሚበቃ እንዳልሆነ ይጠቀሳል።
ብዙዎቹ በየቀኑ በሚሊዮን ሚቆጠር ብር ሲገባ ሲወጣ የሚውልበትን ባንክ እየጠበቅን የምንቀበለው ክፍያ ለቤት ኪራይ የመክፈል አቅም ያለው አይደለም ፡፡
ደግሞም ኤጅንሲዎች ከተቋሙ የሚቀበሉት ብር ብዙ ቢሆንም ለእኛ የሚደርሰን ግን እጅግ ያነሰ ነው ሲሉ ኤጀኒሲዎችን ይኮንናሉ።
Comments