የሀይማኖት ምልክቶችን የሚያንቋሽሹ እና ንፁሀን የሚገድሉ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ ካልተደረገ ለከፋ ግጭት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነገረ
TRACK

የሀይማኖት ምልክቶችን የሚያንቋሽሹ እና ንፁሀን የሚገድሉ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ ካልተደረገ ለከፋ ግጭት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነገረ

Avatar

ጥቅምት 28 2018

የሀይማኖት ምልክቶችን የሚያንቋሽሹ እና ንፁሀን የሚገድሉ ሰዎች በህግ እንዲጠየቁ ካልተደረገ ለከፋ ግጭት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነገረ።

በአደባባይ፣ በጎዳናዎች የሚደረጉ ስብከቶችን ጨምሮ የሀይማኖት ዶግማዎችን የሚያንቋሽሹ እና የሚያነውሩ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚረዳ ስርዓት ለማበጀት ወይይት ተጀምሯል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ጉዳይዎች ቢሮ፣ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በሰላም ጉዳይ ላይ በትናንትናው እለት ተወያይተዋል።

አንድ የውይይቱ ተሳታፊ ህጻናትን ጨምሮ ንጹሃን እየተገደሉ ነው፡፡ ይህን ወንጅል የሚፈጽሙ አካላት ለምንድነው በህግ የማይጠየቁት፣ መቼስ ነው የሚቆመው ሲሉ ጠይቀዋል።

Comments

Avatar