TRACK
በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን ጠየቀ
ጥር 5/2018
በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት በባንክ ብድር ተገንብተው በጦርነቱ የወደሙ ፕሮጀክቶች እዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ጠየቀ፡፡
የትግራይ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት የክልሉ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ብድር ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ማለትም ከ2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ከነበረበት 32 ቢሊዮን ከነወለዱ አሁን ከ80 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል ብሏል፡፡
ምክርቤቱ በክልሉ ለንግድ እና ኢንቨስትመንት የተወሰዱ የባንክ እዳዎች የንግዱ ማህበረሰብ መክፍል ስለማይችል ከፕሪቶሪው የሰላም ስምምነት በኋላ የመክፈያ ጊዜ ገደብ ለ18 ወራት ተራዝሞለት እንደነበር የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ በሪሁ ሃፍቱ ተናግረዋል፡፡
Comments