ሰኔ 20 2017
በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰት በ69.8 በመቶ ቀንሷል ተባለ።
በሌላ በኩል የደንብ ጥሰቶችን ፈፅመው ከተገኙት ውስጥ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናገረ።
በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰት ከፈፀሙ ሰዎች በተያዘው በጀት ዓመት 11 ወራት የተሰበሰበው ቅጣት ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ከግለሰቦች እና ከተቋማት የተሰበሰበ ነው ተብሏል፡፡
ይህንን የሰማነው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።
Comments
awesome. greetings from cape town