ጥቅምት 18፣2017
ባለፈው አንድ ዓመት በ3 ከተሞች ብቻ ከ61 በላይ ሕፃናት ተጥለው ተገኝተዋል ተባለ፡፡
ከመካከላቸው አምስቱ ህይወታቸው ያለፈ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው አንድ ዓመት በተሰበሰበ መረጃ በጅማ ከተማ ብቻ ከ50 በላይ ህፃናት ተጥለው ተገኝተዋል፡፡
በዚሁ ከተማ ሌሎች 3 ህፃናት ደግሞ ተገድለው በፌስታል ተጠቅልለው መገኘታቸውን የጅማ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ለኮሚሽኑ ተነግሯል፡፡
Comments