በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የመንገድ ጥገና ስራዎች
TRACK

በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የመንገድ ጥገና ስራዎች

Avatar

ግንቦት 8 2017

በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የመንገድ ጥገና ስራዎች ዳግም ወደ ስራ እየተገባ ነው ተባለ።

ይህን ያለው የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ነው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ወራት የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም የሚል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አስታውሷል።

ፕሮጀክቱን በመፈፀም ሂደትም የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎችንም ጭምር የመንገድ ስራ እና ጥገና ስራዎች እየሰራን ነው ብሏል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር በተለይ ለመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ፈታኝ መሆኑን አንስተው ሆኖም በህብረተሰቡ ትብብር ከዚህ ቀደም ተቋርጠው የነበሩ እና አዲስ የያዝናቸው ፕሮጀክቶችን ያለምንም ችግር እየሰራን ነው ብለዋል።

Comments

Avatar