በባህር፣ በየብስ  እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።
TRACK

በባህር፣ በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።

Avatar

መጋቢት 21/2018

በአዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ አስመጪዎች በባህር፣በየብስ እና በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን በሚያወጡበት የጊዜ ገደብ ላይ ለውጥ ተደርጓል።

በባህር እና በየብስ ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ከጉምሩክ መጋዘን ማውጫ ጊዜው ከ15 ቀን ወደ 45 ቀን፤በአየር ተጓጉዘው የሚመጡ እቃዎችን ማውጫ ጊዜ ገደቡ ከ10 ቀን ወደ 30 ቀን ይሻሻላል ተብሏል።

ይህንን የፈቀደው ባለፈው ሳምንት እንደገና ተሻሽሎ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የጉምሩክ አዋጅ ነው፡፡

በአንድ ዲክላራሲዮን ወደ አገር ውስጥ የገቡ እቃዎች በአንድነት መለቀቅ እንዳለባቸውም አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ያስገድዳል።

ይህ ግን ብዙ ጊዜ አስመጪው በገንዘብ እጥረት ምክንያት በእቃዎች ላይ ሊከፍል የሚገባውን ቀረጥ እና ታክስ በአንድነት መክፈል በማይችልበት ጊዜ ኮሚሽኑ እቃዎች ተከፋፍለው ሊለቀቁ እንዲችሉ ሊፈቅድ የሚችል አንቀጽ ታክሎበት ሊወጣ መሆኑም ተነግሯል።

ማሻሻያው ሌሎች ነጥቦችንም በስሩ የያዘ ሲሆን የማሻሻያውን መልካም ጎንና ስጋቱን በተመለከተ
የዘርፉን ባለሙያ ጠይቀናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ቴዎድሮስ ወርቁ

Comments

Avatar