TRACK
‘’በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል’’ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
00:00
ታህሳስ 24/2018
‘’በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል’’ ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የድንበር ቁጥጥር መበርታት እና በሰው አዘዋዋሪ ደላሎች ላይ የሚወስደው እርምጃ ለቁጥር መቀነስ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብሏል፡፡
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ በአዋሳኝ ድንበር የሚደረገውን ህገወጥ ፍልሰት በተመለከተ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመተባበር እየተደረገ ባለው ጥብቅ የቁጥጥር ስራ በርካታ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በመያዝ ተጠያቂ እየሆኑ ነው ብለዋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም በአጎራባች ሀገራት በኩል ይደረጉ የነበሩ በርካታ ህገወጥ ፍልሰቶች እንዲቀንሱ አድርገዋል ይላሉ።
Comments
00:00