TRACK
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ አስገዳጅ መመሪያዎችን በማለፍ ከማርበርግ ቫይረስ ነጻ መሆኗ ተነገረ፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ አስገዳጅ መመሪያዎችን በማለፍ ከማርበርግ ቫይረስ ነጻ መሆኗ ተነገረ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ በሽታ ለመቆጣጠር በተሰሩ ስራዎች ኢትዮጵያ ከቫይረሱ ነጻ መሆኗን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ሀገራት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ደረጃዎችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።
ኢትዮጵያም የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠር የተቀመጠውን አስገዳጅ የአርባ ሁለት ቀናት ከበሽታ ነጻ የመሆን ጊዜ በማጠናቀቋ ዛሬ በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ተሰጥቷታል፡፡
Comments