00:00
የካቲት 26 2017
በኢትዮጵያ ከልብ ህክምና ጋር የተያያዙ ስራዎች ላይ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በመንግስት የሚቋቋሙ ተጨማሪ ማዕከላት ያስፈልጋሉ ተባለ፡፡
በአገሪቱ ብቸኛ የሆነውና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የሚገኘው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ከመንግስት የተወሰኑ ድጋፎች ባገኝም አገልግሎቱን እየሰጠሁ ያለሁት ከዜጎች በሚገኝ ድጋፍና በዓለም አቀፍ ለጋሾች እርዳታ ነው ብሏል፡፡
ማዕከሉ ቋሚ የሆነ በጀት ያልተመደበለትና በሚገኝ ድጋፍ ብቻ የልብ ህክምና አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡
ከልብ ህመም ጋር የተያያዙ አብዛኛዎቹ ህመሞች ህክምና በሃገር ቤት ባለሙያዎች እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ሜዲካል ዳይሬክተር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሄሌዘር ሀይሌ ነግረውናል፡፡
አብዛኛዎቹ የህክምና መሳሪያዎች ከውጭ መምጣታቸው፣ ግብዓቱን የሚያመጣው አካል የመረጃ ስርጭቱ ላይ የተወሰነ ችግር አለው የህክምና ዓይነቶቹ እዚህ አገር እንደማይሰራ ተደርጎ የሚቀርብበት ሂደት አለ እሱ መቅረት አለበት ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የማይሰሩ ውስን የሆኑ የልብ ንቅለ ተከላ ዓይነት ችግሮች ካልሆነ በስተቀር በአብዛኛው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መሰራት የሚችሉ ናቸውም ብለዋል፡፡
Comments
00:00