TRACK
የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር ከተናጠል ውይይት ይልቅ ራሱን ችሎ የሚሰራ ቀጠናዊ ተቋም ቢመሰረት ይበጃል የሚል ሀሳብ ቀረበ
ሰኔ 11 2017
የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር ከተናጠል ውይይት ይልቅ ራሱን ችሎ የሚሰራ ቀጠናዊ ተቋም ቢመሰረት ይበጃል የሚል ሀሳብ ቀረበ፡፡
እንዲህ ዓይነቱ ተቋም መመስረቱ አባል ሀገራት ያለባቸውን የፖሊሲ እና ሌላውንም የአሰራር ችግር አናበው መስራት እንዲችሉ ያግዛችዋል የተሻለ ትብብርም በቀጠናው ይፈጥራል ተብሏል፡፡
የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ሃብቱን በትብብር ማልማት እና መጠቀም በሚችሉበት ሀሳብ ዙሪያ የሚመክረው የአፍሪ ራን አራተኛው ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የቀጠናውን ሀገራት በኤሌክትሪክ መስመር ማስተሳሰር የዘንድሮ መነጋገሪያ ሀሳብ ነበር፤ ዶክተር ግዛቸው አስራት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄነራል ናቸው፡፡
Comments