ጥር 28/2018
በአሁኑ ወቅት በቂ የነዳጅ ምርት ቢኖርም የነዳጅ አቅራቢዎች በየቀኑ ወደ አዲስ አበባ መግባት ያለበትን መጠን እያስገቡ አይደለም ተብሏል።
በዚህም ምክንያት ከሰሞኑ ነዳጅ ለመቅዳት በማዲያዎች የሚደረጉ ረጃጅም ሰልፎች ተስተውለዋል ያለን የዘርፉን ግብይት የሚቆጣጠረው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነው።
በከተማዋ ባሉ 125ቱም ማደያዎች ምን ያህል ነዳጅ በየትኛው ማደያ አለ የሚለውን እለታዊ መረጃ በማሰራጨት ቁጥጥር የሚያደርገው ቢሮው በቂ ነዳጅ አለ ለማለት በቀን ከ2.8 ሚሊዮን ሊትር በላይ ናፍጣ፣ ቤንዚን 2 ሚሊዮን ሊትር መኖር አለበት፤ አሁን ያለው 2.5 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ነው ፤ ለዚህ ነው በየቦታው ሰልፍ የበዛው ሲሉ በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ አስረድተዋል።
Comments