የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን አጀንዳ በሰበሰብኩባቸው ክልሎች ያልተሳተፉ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም አለ፡፡
TRACK

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን አጀንዳ በሰበሰብኩባቸው ክልሎች ያልተሳተፉ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም አለ፡፡

Avatar

ነሐሴ 23፣2016

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን አጀንዳ በሰበሰብኩባቸው ክልሎች ያልተሳተፉ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም አለ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ላይ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሆነው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጀንዳ አሰባሰብ ሒደት ላይ ሁሉም ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡

የምክክሩ ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ፤ ኮሚሽኑ በሀገር ደረጃ ምክክር የሚደረግባቸው አጀንዳዎች የማሰባሰብ ሂደት በሲዳማ ክልል እየተካሄደ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

በመጪው ቅዳሜ ደግሞ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት እንደሚጀመር ቃል አቀባዩ ነግረውናል፡፡

‘’እስካሁን አጀንዳ በተሰበሰበባቸው 3 ክልሎች በምክክሩ ያልተሳተፉ የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም’’ ያሉት አቶ ጥበቡ ታደሰ ይህም ምክክሩ በታሰበው ልክ እየሄደ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

Comments

Avatar