ታህሳስ 14/2018
የስራ ገበያው የተማረ እና ብቁ የሰው ሀይል ለማግኘት እየተቸገረ መሆኑን በተደጋጋሚ ይነገራል።
ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት ከሚነሱ ችግሮች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት የትምህርት ተቋማት ሲያሰለጥኑ ገበያው በምን ዘርፍ የሰለጠነ ሰው ሀይል ያስፈልገዋል ብለው ተማሪዎቻቸውን አለማሰልጠናቸው እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡
ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመማር ሲገቡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በምን ሙያ የሰለጠነ የሰው ሀይል ያስፈልገዋል የሚለውን ሳያጠኑ ነው ቀጥታ የሚገቡት ብለዋል ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያ።
ዩኒቨርሲቲዎቹም ቢሆኑ ሀገሪቱ በምን ዘርፍ ምን ያህል የሰለጠነ የሰው ሀይል ያስፈልጋታል የሚለውን ጉዳይ ትኩረት ሲሰጡበት አይስተዋልም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እቅድ እና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ባልደረባ ደሞዜ ደገፋ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
Comments