''የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ተገልጋዩን ጫና ውስጥ የሚከትት፤የሃገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት የሚጥስ ነው'' በሚል በፓርላማው ጥያቄ አስነሳ
TRACK

''የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ተገልጋዩን ጫና ውስጥ የሚከትት፤የሃገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት የሚጥስ ነው'' በሚል በፓርላማው ጥያቄ አስነሳ

Avatar

ሚያዝያ 13/ 2018

ተጨማሪ የአቭየሽን ክፍያ መክፈልን የሚያስገድደው የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ተገልጋዩን ጫና ውስጥ የሚከትት፤የሃገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት የሚጥስ ነው፤ በሚል በፓርላማው ጥያቄ አስነሳ፡፡

አዋጁ በስራ ላይበ ሲውል እያንዳንዱ የአየር መንገድ ተጓዥ ከ30 እስከ 156 ብር የደረሰ ተጨማሪ ክፍያ የሚጠየቅበትን አሰራር የሚዘረጋ ነው፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ላለፉት 20 ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን ነባሩን የአቪየሽን ሴኩሪቲ አዋጅ ለማሻሻል በውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዮች ቋሚ ኮሚቴና በከተማ መሰረተልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበለት የረቂቅ አዋጁ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም ወቅት በአዋጁ የተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ ከፓርላማ አባላት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

Comments

Avatar