በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን በተመለከተ ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቋል ተባለ
TRACK

በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን በተመለከተ ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቋል ተባለ

Avatar

ምዕራፍ - የካቲት 19፣2016

በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን በተመለከተ ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቋል ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ወረቀት እና የወረቀት ውጤቶችን የሚያመርቱ እንዲሁም የማሸግ እና ማተም አገልግሎቶች የሚሰጡ የተለያዩ ፋብሪካዎች አሉ ።

የእነዚህ ፋብሪካዎች አቅም ግን በሀገር ውስጥ ካለው ፍላጎት ጋር ሲነሳሰር አነስተኛ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በዚህም ምክንያት ምርቶቹ በአብዛኛው ከውጪ ይገባሉ ሲሉ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት እና ግብአት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ነግረውናል።

ፍላጎቱን የሚሸፍን ወረቀት በሀገር ውስጥ እንዲመረት መንግስት ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግ የተናገሩት አማካሪው፤ በዚህ ዙሪያ ያደረጋቸው አንዳንድ ጥናቶችም አልቀዋል ብለዋል፡፡

የፐልፕ፣ ወረቀትና ፓኬጅንግ አምራቾች ማህበር ከሠሞኑ እንደተመሰረተም ሠምተናል፡፡

የማህበሩ መመስረት መንግስት ዘርፉ እንዲሻሻል የሚያሰራውን ስራ ያግዛል ሲሉም አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሣ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የወረቀት_ምርት #ፐልፕ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar