ጥር 12፣ 2017
የአዕምሮ እድገት ውስንነት እና የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆቻችንን ይዘን ወደ መንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ስንሄድ፤ ትምህርት ቤቶቹ እንቀበልም ይሉናል በማለት ወላጆች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ከ85 እስከ 90 በመቶዎቹ የትምህርት እድል አያገኙም ሲል ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ ተናግሮ ነበር፡፡
የአዲስ አባባ አካል ጉዳተኞች ማህበርም ት/ት ቤቶች ልጆቹን አንቀበልም በማለታቸው ወላጆች እየተማረሩ ናቸው ብሎናል፡፡ የማህበሩ ፕሬዚደንት ወይንሸት ግርማ (ዶ/ር) እነዚህ ወላጆች ተሰብስበው ክስ ቢመሰርቱ ተቀባይነት አላቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ታዳጊ ሀያት ከድር፤ ‘’አንድንት የአዲስ አባባ አካል ጉዳተኛ ህጻናት ማህበር’’ ሰብሳቢ ናት፡፡ አካ ጉዳተኛ ህጻናትና ታዳጊዎች የበዙ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ታነሳለች፡፡ ትምህርት ቤት የገቡትም ቢሆን የመማሪያ ቁሳቁሶች ስለማይሟሉላቸው በተገቢው ትምህርቱን ይማራሉ ማለት እንደማይቻልም ትናገራለች፡፡
Comments