ሐምሌ 25፣2016
የኢ-ኮሜርስ ፖሊስ ወደ ስራ ሲገባ በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም መንገዶችና ቤቶች ግልፅ የሆነ የአቅጣጫ መጠቆሚያ እንዲኖራቸው ይደረጋል ተባለ፡፡
ወደ ዲጂታሉ ዓለም በፍጥነት እተጓዘች ያለችው ኢትዮጵያ የኦላይን ንግድን ህጋዊ በማድረግ፤ ልክ እንደ መደበኛው የንግድ ሥርዓት ሁሉ በየትኛውም የሃገሪቱ ማዕዘናት ያሉ ሰዎች ኢንተርኔትን በመጠቀም ካሉበት እያዘዙ እንዲገበያዩ ገበያውን ክፍት አደርጋለሁ ብላለች፡፡
ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቀድሞ መስተካከል ያለበትና እንደሃገር ወደኋላ ከቀረንባቸው ነገሮች አንዱ ቤቶችና መንገዶች ግልፅ የሆነ የአቅጣጫ መጠቆሚያ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡
ይህንን ለማድረግ አቅጣጫዎችን መዝግቦ በኦላይን የሚያስቀምጥ የዲጂታል ማፕ (በኤሌክሮኒክ መላ የተሰናዳ የአቅጣጫ መጠቆሚያ ካርታ) እንደሚዘጋጅ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢትዮጵያ ማህበር ምክትል ሀላፊ አቶ ባህሩ ዘይኑ ነግረውናል፡፡
ሸገር ያነጋገራቸው በኦላይን ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችም የቤቶች እና የመንገዶች አቅጣጫ በግልፅ ስለማይታወቅ በኦላይን የምንቀበላቸውን ትዕዛዞች ለማድረስ ተቸግረናል ይላሉ፡፡
Comments