ጥቅምት 18፣2017
በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገራቸው የሚወጡ ስደተኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው ተባለ፡፡
18 ዓመት ያልሞላቸው ህፃናት ጭምር በህገወጥ መንገድ ከሀገር እንደሚወጡ ተነግሯል፡፡
ይህንን የተናገረው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
በአመትም ከ150,000 እስከ 200,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሀገር ይወጣሉ የተባለ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍልሰቱ ጨምሯል ይላሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ፡፡
Comments