ሚያዝያ 16 2017
በትግራይ ክልል ያሉ ተፈናቃዮች ብዛት 1ሚሊዮን መድረሱንና ተፈናቃዮቹ ከዚህ ቀደም ከነበረው የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የእምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
የተፈናቃዮቹ ችግር ከነበረው ተባብሶ ለበሽታና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ከህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሰምተናል፡፡
የቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ እምባዬ ምን አሉ?
በትግራይ ክልል ያሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ በዚህ ዓመት በተቋሙ ቁጥጥር ተደርጎ የተፈናቃዮቹ ቁጥር 1ሚሊዮን መድረሱ ታውቋል፤ ዘንድሮ የሱዳኑን ጦርነት ሸሽተው የመጡ እንዲሁም ወደ ቀያቸው ተመልሰው የነበሩ ተፈናቃዮች፤ በተለያየ ምክንያት ወደ መጠለያዎቹ ዳግም የተመለሱ ተፈናቃዮች ቁጥር ሲደማመር ነው የተፈናቃዮቹ ብዛት 1ሚሊዮን የደረሰው፡፡
ተፈናቃዮቹ የውሃ አቅርቦት የላቸውም፤ ከዚህ ቀደም በነብስ ወከፍ 15 ኪሎ ግራም እህል ይሰጣቸው ነበር አሁን ግን እርዳታው ወደ 9 ኪሎ ግራም ወርዷል፤ የምግብ እጥረቱ ያመጣቸው የተለያዩ በሽታዎች በመኖራቸው ነው፤በዚህም ምክንያት ሞት ተከስቷል ብለውናል አቶ ፀሃዬ፡፡
Comments