በህንጻ ግንባታ ላይ የደህንነት መከላከያ ባላሟሉ አስገንቢዎች ላይ እስከ እስራት የሚያደርስ ህግ መዘጋጀቱ ተሰማ
TRACK

በህንጻ ግንባታ ላይ የደህንነት መከላከያ ባላሟሉ አስገንቢዎች ላይ እስከ እስራት የሚያደርስ ህግ መዘጋጀቱ ተሰማ

Avatar

ሰኔ 26፣ 2016

በህንጻ ግንባታ ላይ የደህንነት መከላከያ ባላሟሉ አስገንቢዎች ላይ እስከ እስራት የሚያደርስ ህግ መዘጋጀቱ ተሰማ።

አዲሱ ህግ ስራ ላይ ሲውል በህንጻ ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ የደህንነት ችግሮች እና ስጋቶችን ይቀርፋልም ተብሎለታል።

በህንጻ ግንባታ ላይ በሚስተዋሉ የጥንቃቄ ጉድለት፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት እየጨመረ መምጣቱ አዲሱ ህግ እንዲወጣ ምክንያት ሆኗልም ተብሏል።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ መዲና አህመድ፤ ህንፃዎች በሚገነቡበት ሰዓት በአካባቢው እና በህብረተሰቡ ላይ ስጋት በሆነ መልኩ በሚገነቡና ለሰራተኞቻቸው ጭምር የደህንነት መከላከያ ግብአቶች ሳያሟሉ በተገኙ አስገንቢዎች ላይ ከፈቃድ መቀማት እስከ እስራት ድረስ እንዲቀጡ በህጉ ተቀምጧል ሲሉ ነግረውናል።

Comments

Avatar