ከ2 ሳምንት በኋላ 35 የቻይና ኢንተርፕራይዞች አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሏል
TRACK

ከ2 ሳምንት በኋላ 35 የቻይና ኢንተርፕራይዞች አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሏል

Avatar

ሚያዝያ 22፣2016

ወጣት ኢትዮጰያዊያን ስራ ፈጣሪዎችን በተለያየ መንገድ ለማገዝ በቻይና ቢሮ ከፍቼ በብርቱ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ተናገረ፡፡

የዚህ ቢሮ በቻይና መከፈት፤ ለወጣት ኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣዎች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ጋር የገበያ ትስስር እንዲኖራቸው ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተለይም ቻይና ካፍሪካ ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት(China-Africa trade and investment promotion) ላይ ኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች ግንዛቤ ኖሯቸው በንቃት እንዲሳተፉ ያግዛቸዋልም ተብሏል፡፡

በቻይና ቢሮ መክፈት ያሰፈለገውም ቻይና በዘርፉ የምታደርገው እንቅስቃሴ ሰፊ በመሆኑ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚደንት ሳሚያ አብዱልቃድር ነግረውናል፡፡

በውጭ ሀገራትና በሀገር ቤት በቢዝነስ ኢንቨስትመንት የመሳተፍ እድል ማግኘት፣ የገበያ ድርሻ፣ የቴክኖሎጂ እና ሌሎች ልምዶችን መቅሰም፤ ወጣት ስራ ፈጣሪዎቹ ይጠቀሙባቸዋል ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ናቸው፡፡

በሌላ በኩል፤ ከ2 ሳምንት በኋላ 35 የቻይና ኢንተርፕራይዞች አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሏል፡፡

እነዚህ እንተርፕራይዞች ከማህበሩ እና ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ ውጥን መያዙንም የማህበሩ ፕሬዚደንት ሳሚያ አብዱልቃድር አውርተውናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማህበሩ በየጊዜው ይፋ የማደርጋቸው ሌሎች ስራዎችም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን(VISA) ጋር እየሰራሁት ያለሁትም ከነዚህ ውስጥ ተቃሽ ነው ሲል ማህበሩ ለሸገር አስረድቷል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ

Comments

Avatar