ግንቦት 14 2017
ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ገንዘብ ከአራት በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል።
ውሳኔው ጥሩ የሚባል ቢሆንም የኢትዮጵያ ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች እንዲያስከፍሉ የተቀመጠው ጣሪያ አሁንም ቢሆን ትንሽ እንዳልሆነ አንድ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ተናግረዋል።
ወደ ውጪ ሀገር ለሚሄዱ የግል ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ ወደ አስር ሺህ ዶላር እንዲያድግ የተላለፈው ውሳኔም የውጭ ምንዛሪ ተመን ገበያ መር ይሁን ከመባሉ ጋር የተገናኘ ነው ብለዋል።
ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ገንዘብ ከአራት በመቶ እንዳይበልጥ መወሰኑን ብሄራዊ ባንክ ይፋ አድርጓል።
ጥቃቅን የአገልግሎት ወጪዎችን ደግሞ እንዲያስቀሩ መወሰኑን ባንኩ ይህንኑ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ገንዘብ እስከ አስር በመቶ ደርሶ እንደነበር የሚያስታውሱት፤ የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶክተር ቴዎድሮስ መኮንን ይህም ከሌሎች ሀገራት አንጻር ከፍተኛ የሚባል እንደሆነ ተናግረዋል።
Comments