ሚያዝያ 29 2017
የደረጃ ’’ሀ’’ እና ’’ለ’’ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ሲያሳውቁ የሂሳብ መዝገብ እንዲያቀርቡ ሊገደዱ ነው፡፡
የተደራጀ የሂሳብ መዝገብ እንዲያቀርቡ በህግ ቢገደዱም 55,000 ግብር ከፋዮች ምንም አይነት የሂሳብ መዝገብ እያቀረቡልኝ አይደለም ሲል የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ፡፡
ስለሆነም ቢሮው ከዚህ በኋላ አልታገሳቸውም፤ ከሃምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ ’’ሀ’’ እና ’’ለ’’ግብር ከፋዮች ያለ ሂሳብ መዝገብ አይስተናገዱም ብሏል፡፡
ከጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኛው ግብር የሚከፈለው በቁርጥ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ግን ወደ ማስገደድ እንሸጋገራለን ያሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ናቸው፡፡
Comments