በሱዳን በተቀሰቀሰው ጦርነት የተነሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን በአማካይ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ለማውጣት ተገዶ እንደነበረ ተሰማ
TRACK

በሱዳን በተቀሰቀሰው ጦርነት የተነሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን በአማካይ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ለማውጣት ተገዶ እንደነበረ ተሰማ

Avatar

ጥቅምት 12፣2016

በሱዳን በተቀሰቀሰው ጦርነት የተነሳ ሀገሪቱ የአየር ክልሏን ለበረራ ዝግ በማድረጓ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለይ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የሚያደርገውን በረራ በኬንያ እና በዩጋንዳ ለማድረግ በመገደዱ በቀን በአማካይ ከ6 ሚሊዮን ብር ለማውጣት ተገዶ እንደነበረ ተሰማ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ግን የደቡብ ሱዳንን የላይኛውን የአየር ክልል አማራጭ የአደጋ ጊዜ የበረራ መስመርነት አየር መንገድ እየተጠቀመ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በሱዳን ጦርነት የተነሳ ሀገሪቱ የአየር ክልሏን ለበረራ ዝግ በማድረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀገር ውጪ ለሚያደርገው በረራ ባያፍታቱትም ብዙ ችግር እንዳጋጠመው ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአየር ትራፊክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ አበራ የሱዳን የአየር ክልል መዘጋት አየር ክልሉን ለሚጠቀሙ አየር መንገዶች ከፍተኛ ወጪ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን በአማካይ 94,000 ሊትር ነዳጅ ወይንም በገንዘብ ሲሰላ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲያወጣ ተገዶ ነበር ብለዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments

Avatar