00:00
ሐምሌ 24 2017
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ከናካቴውም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲም ሳይሄዱ እንዲቀሩ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ5 ዓመት በፊት የጀመረው ‘’የቃል ኪዳን ቤተሰብ’’ የሚለው አሰራር ግን ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ተማሪዎች ሁሉ እንዲቀበል፣ ተማሪዎችም በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት እንዳያቋርጡ አድርጓል ተብሏል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቃል ኪዳን ልጅና ወላጅ አድርጎ ያገናኛቸው ሰዎች ታሪክም ይህን ይመሰክራል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments
00:00