ባንኮች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ሰምተናል
TRACK

ባንኮች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ሰምተናል

Avatar

ታህሳስ 24፣2017

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከቀናት በኋላ በነባሩም ሆነ አዳዲስ ውለታ የሚገቡትን ተበዳሪዎች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሸገር ሬዲዮ ከታማኝ የባንክ ምንጮቹ ሰምቷል፡፡

ይህም የብድር የወለድ ምጣኔው እስከ 20 እና 22 በመቶ ይደርሳል እንደማለት ነው፡፡

ከዓመታት በፊት የነበረውን የገንዘብ የመግዛት አቅም እና የኢኮኖሚውን ሁኔታ እንዲሁም የገቢ መጠናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከባንክ በመበደር ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ሆኑ ቤት የገዙ ተበዳሪዎች በተበደሩት ወለድ ላይ ከ3 እስከ 5 በመቶ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

Comments

Avatar