በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሚፈፀሙ እገታዎች ስጋት ውስጥ ወድቀናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
TRACK

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሚፈፀሙ እገታዎች ስጋት ውስጥ ወድቀናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

00:00

ጳጉሜ 5፣2016

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሚፈፀሙ እገታዎች ስጋት ውስጥ ወድቀናል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በጎንደር ከተማ የፒያሣ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሸረፈዲን ኢብራሂም ‘’ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ መንቀሳቀስ ቅንጦት ሆኖብን ሳለ አሁን ደግሞ ከቤታችን መታገት መጣብን’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘’ሰው መጠየቅ፣ ሀዘን መድረስ እና ወደ አምልኮ ስፍራ መሄድ በእገታው ምክንያት ቀርቷል’’ ብለዋል፡፡

‘’በከተማ የሚኖረው ነዋሪ ሳይቀር በእገታ ስጋት ውስጥ ወድቋል’’ የሚሉት አቶ ሸረፈዲን ‘’ነዋሪው ሲመሽ መስጋት፣ ሲነጋ ደግሞ መደሰት ውስጥ ነው’’ ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

Comments

00:00