በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበሩ ከተባሉ ኢትዮጵያዊያን መካከል አድራሻቸው የተገኘ ዜጎችን እንዲመለሱ ማድረጉ ተነገረ
TRACK

በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበሩ ከተባሉ ኢትዮጵያዊያን መካከል አድራሻቸው የተገኘ ዜጎችን እንዲመለሱ ማድረጉ ተነገረ

Avatar

ህዳር 6፣ 2017

በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እና እንደባሪያ ሊሸጡ ነበሩ ከተባሉ ኢትዮጵያዊያን መካከል አድራሻቸው የተገኘ ዜጎችን መንግስት ወደ ሀገር እንዲመለሱ ማድረጉ ተነገረ፡፡

እስካሁንም 31 ሰዎች አድራሻቸው መታወቁ ተሰምቷል፡፡

ባለፉት ወራት በህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የታየውና የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ስምሪት ወዳልፈረመባት ማይናማር ዜጎች ተወስደው እንደባሪያ ይሸጡ እንደነበር ሲነገር ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በማይናማር ኤምባሲ ስለሌለው በአካባቢ ሀገራት ባሉ ዲፕሎማቶች አማካይነት በተሰራ ስራ አድራሻቸው የተገኙ ዜጎችን ማስመለስ መቻሉን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በማይናማር የሚገኙ እና አድራሻቸው ከታወቁ ዜጎች በተጨማሪ በሳውዲ አረቢያና በቤይሩት በአስቸጋ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን በተመሳሳይ መንግስት ወደ ሀገር እንዲመለሱ አድርጓልም ተብሏል፡፡

Comments

Avatar