የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ህጎች ቢወጡም በአግባቡ አለመተግበራቸው  በትራፊክ አደጋ የሚደርሰው ጉዳት እንዲያሻቅብ እያደረገው ነው ተባለ
TRACK

የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ህጎች ቢወጡም በአግባቡ አለመተግበራቸው በትራፊክ አደጋ የሚደርሰው ጉዳት እንዲያሻቅብ እያደረገው ነው ተባለ

Avatar

ሐምሌ 23፣2016

የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል መቆጣጠሪያ ህጎች ቢወጡም በአግባቡ አለመተግበራቸው ግን በየዕለቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳት እንዲያሻቅብ እያደረገው ነው ተባለ፡፡

ለዚህም ህግ ከማውጣት ባለፈ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንገድ ተጠቃሚዎች ስነ ምግባር ላይ ይበልጥ መስራት እንዳለበት ተነግሯል፡፡

በየዕለቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ብዙዎች የሞት እና የአካል ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ በአንድ ቀን ብቻ በዕለት እስከ 5 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ፤ ብዙዎችም ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ ለዚሀም በትራፊክ አደጋ ላይ የሚከወኑ የመንገድ ደህንነት ስራዎች ሊበረቱ ይገባል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ት/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ላይ በተለይ ለአዲስ አበባ መፍትኤ የተባሉ ጉዳዮች በተመለከተ ጥናት ተከውኗል፡፡

Comments

Avatar