''አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅርቦች ችግር እንዳይገጥም እየሰራሁ ነው'' የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን
TRACK

''አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅርቦች ችግር እንዳይገጥም እየሰራሁ ነው'' የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን

00:00

ጳጉሜ 1፣2016

ቀናት የቀሩትን የ2017 መባቻ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅርቦች ችግር እንዳይገጥም እየሰራሁ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን ተናገረ።

በአላት ሲቃረቡ የሚፈጠረውን የአቅርቦት ችግርን ለመቀነስ ኮሚሽኑ አስቀድሜ ስራዎችን እየከወንኩ ነው ብሏል።

ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

የግብርና ምርቶች፣ የፋብሪካ ውጤቶች እና ሌሎች ግብአቶችንም ለነዋሪው በሚበቃ መልኩ በማከማቻ መጋዘኖች እንዲቀመጥ አድርጌአለሁ ብሏል።

በተለይ የግብርና ምርቶችን በከተማዋ የሚገኙ 11 ዩኒየኖች ከአምራቾች በቀጥታ በማምጣት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ እየተደረገ ነው ያሉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ልእልቲ ግደይ ወደ ከተማዋ የሚገባው ፍጆታም ከነሀሴ 27 ጀምሮ በባዛሮች ላይ እየቀረበ ነው ነው ብለዋል፡፡

Comments

00:00