አብዛኞቹ የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ የመዘመን ፍላጎት አያሳዩም ተባለ
TRACK

አብዛኞቹ የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ የመዘመን ፍላጎት አያሳዩም ተባለ

Avatar

የካቲት 11 2017

አብዛኞቹ የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ የመዘመን ፍላጎት አያሳዩም ተባለ፡፡

በቼክ እና በደብዳቤ መፈረም እንደ ትልቅ ስልጣን የሚቆጥሩ ባለስልጣናትም አሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡

ተቋማቱ የክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ ቶሎ ከመቀበል ይልቅ በነበረው አሰራር መቆየትን ይመርጣሉ ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር ነግሮናል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ወጪ ለመቀነስ፣ ለቅልጥፍና፣ እና ለግልፀኝነት ይረዳ ዘንድ የመንግስት ተቋማት የክፍያ ስርዓትን በማዘመኑ በብርቱ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በዚህ ሂደት ግን እየገጠሙ ያሉ ችግሮች መኖራቸውን በገንዘብ ሚኒስቴር የትሬዠሪ እና የመንግስት ሂሳብ መምሪያ ሀላፊ ነጠሩ ወንድወሰን ነግረውናል፡፡

መንግሰስት በብርቱ እየሰራሁበት ነው ያለው ይህ የዲጂታል ስርዓት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉትም ሀላፊዋ አስረድተዋል፡፡

በስርዓቱ ትግበራ ወቅት እየገጠሙን ነው ካሏቸው ችግሮች መካከል አንደኛው ተቋማት ቀድሞ ሲሰሩበት ከነበረው አሰራር ጋር ለመላቀቅ ማስቸገራቸው ነው ተብሏል፡፡

በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል በበቂ አለመኖርም ሌላው ስራውን የፈተነው ጉዳይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ብዙ መስሪያ ቤቶች አዲሱ የክፍያ ስርዓትን ከመጠራጠርና ካለማመን የተነሳ፣ ትላልቅ በመንግስት ደረጃ ለሚፈጸሙ ክፍያዎች ራሱ አስር ብር፣ መቶ ብር እያስተላለፉ ነው እየለመዱት እየመጡ ያሉት ብለዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በምህረት ስዩም

Comments

Avatar