ሚያዝያ 2 2017
የስንዴ ዱቄት በተለያዩ ንጥረ ነገሮች አበልፅጌ ለገበያ እያቀረብኩ ነው ሲል ‘’ዲና የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ’’ ተናገረ፡፡
ተጨማሪም የጤፍ፣ የቦቆሎ እና የተለያዩ ዱቄቶችን እንደሚያቀርብ የተናገረ ሲሆን የስንዴ ዱቄት በቀን ከ1900 ኩንታል በላይ፣ 1,000 ኩንታል በቆሎ እና 600 ኩንታል የጤፍ ዱቄት እንደሚያመርት ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የዘይትና የስንዴ ዱቄት በቫይታሚንና በሌሎች ንጥረ ነገሮች ለማበልፀግ አስገዳጅ መመሪያ ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው፡፡
Comments