የገቢ ግብር እንዲቀንስ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ጥያቄው ሰሚ አላገኘም
TRACK

የገቢ ግብር እንዲቀንስ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ጥያቄው ሰሚ አላገኘም

00:00

ግንቦት 19 2017

የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብር እንዲቀንስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና በሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጭምር በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ጥያቄው ሰሚ አላገኘም፡፡

ሰራተኛም የሚከፍሉት የገቢ ግብር ከፍተኛ በመሆኑ ለነገ መቆጠብ እና ጥሪት መያዝ ቀርቶ በልተው ለማደር እንኳን መቸገራቸውን ያነጋገርናቸው ሰራተኞች ያስረዳሉ፡፡

ለመሆኑ መንግስት ለምን የሰራተኛውን የገቢ ግብር ቅነሳ ጥያቄ መመለስ አልፈለገም? የገቢ ግብሩ ቢስተካከል መንግስት የሚያጣው ምንድነው ? የጎረቤት አገራት ልምድስ እንዴት ያለ ነው?

ለመጠናቀቅ 40 ቀናት በቀረው በጀት ዓመት ወደ 900 ቢሊዮን ብር ከቀረጥ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ያለው መንግስት 50 ቢሊዮን ብሩን ከመንግስት እና ከግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ለመሰብስብ እየሰራ መሆኑን የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት በለሙያው አቶ መርዕድ ፈቅረዮሃንስ ያስረዳሉ፡፡

Comments

00:00