ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚወጡ የአደጋ መከላከል ቅድመ ትንበያዎችን ወደ ተግባር የመቀየር ችግር አለባት ተባለ
TRACK

ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚወጡ የአደጋ መከላከል ቅድመ ትንበያዎችን ወደ ተግባር የመቀየር ችግር አለባት ተባለ

Avatar

ግንቦት 13 2017

ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚወጡ የአደጋ መከላከል ቅድመ ትንበያዎችን ወደ ተግባር የመቀየር ችግር አለባት ተባለ፡፡

ይህ የሚሆነው የተግባር ስራው ብዙ ገንዘብ መመደብን የሚፈልግና ውድም ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡

ይህን ያለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ወይንም ኢጋድ የአየር ጠባይ ትንበያ ትግበራ ማዕከል ነው፡፡

ኢትዮጵያ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ሙሉ ለሙሉ እንዳትከውን አድርጓታል ተብሏል፡፡

የኢጋድ የአደጋ መከላከል ስራ አስኪያጅ አህመድ አምድይሁን(ዶ/ር) ኢትዮጵያን እና የኢጋድ አባል አገራትን የአየር ሁኔታ በተመለከተ በአመት ሶስት ጊዜ የትንበያ መረጃዎች እና ቅድመ አደጋ መከላከል ማስጠንቀቂያዎችን እናወጣለን ብለዋል፡፡

Comments

Avatar