TRACK
የማህበራዊ ትስስር እንዳለ በርካታ ማሳያዎች ቢኖሩም ዛሬም ብሔር መሰረት አድርገው፣ ሃይማኖት መርጠው የሚፈጠሩ ግጭቶች እዚም እዛም አልፎ አልፎ ይከሰታሉ
ሐምሌ 18 2017
የኢትዮጵያዊያን መካከል ጠንካራ የማህበራዊ ትስስር እንዳለ በርካታ ማሳያዎች ቢኖሩም ዛሬም ድረስ ብሔር መሰረት አድርገው፣ ሃይማኖት መርጠው የሚፈጠሩ ግጭቶች እዚም እዛም አልፎ አልፎ ይከሰታሉ፡፡
በኢዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ስነሰብ (Social Antropology) መምህር ሆነው ለበርካታ ዓመታት ያስተማሩት፣ በመስኩ ላይም ጥናት የሰሩት ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) በክርስትና የአብነት እና በእልምና ደግሞ የደረሳ ተማሪዎችን ማሳያ አድርገው ያነሳሉ፡፡
ሁለቱም የሃይማኖት ትምህርት ተማሪዎች ጥሩ መምህር አለ፣ የተሻለ እውቀት ይሰጠኛል ብለው ወዳመኑበት አካባቢ ሲሄዱ ከቤተሰባቸው ስንቅ ተቋጥሮላቸው ሳይሆን የሚሄዱበት አካባቢ ማህበረሰብ እንደ ቤተሰብ ይቀበለኛል ብለው በማመን እንደሆነ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡
Comments